
ተቋሙ ከተቋቋመበት ዓላማ ዉስጥ አንዱና ዋናዉ የተለያዩ የፍትህ አካላት ስልጠና መስጠት ሲሆን ለዚህም ቤተ-መጽሐፍት መሰረታዊ በመሆኑ ለሰልጣኞች እና ለሰራተኞች የተለያዩ መጽሐፍትን በውሰት
እና በሶፍት ኮፒ በመስጠት ላይ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ለአካባቢዉ ማህበረሰብ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡
ለተማሪዎች የሁሉም ትምህርት ክፍሎች የመማሪያ መፅሐፍትን በቤተ-መጽሐፍት ዉስጥ በሚገኙ ኮምፒውተሮች በመጫን የመጽሐፍት ችግር ላለባቸዉ ተማሪዎች ችግር በመቅረፍ
ትዉልድን በማነፅ ረገድ የራሱን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡
በቤተ-መጽሐፍት ዉስጥ የሚገኙ ካታጎሪዎች :-
- የፌዴራልና የክልል ህጎች፣
- የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት እና ሰበር ዉሳኔዎች፣
- ጆርናሎች/ጥናቶች ፣ ፖሊሲ እና ስትራቴጅ፣
- የተለያዩ አጋዥ የህግ ነክ መጽሐፍቶች እና የመማሪያ መጽሐፍቶች፣
- መጽሔቶች ፣ ልብ-ወለድ መጽሐፍቶች፣ቀደምት ታሪካዊ መጽሐፍቶች እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡
ምንም እንኳን ቤተ-መጽሃፍቱ የተደራጀው ለተቋሙ ሰራተኞች፣ ሰልጣኞችና ለሕግ ጥናትና ምርምር ባለሙዎች ቢሆንም ነገር ግን አገልግሎታችንን ማስፋትና የተደራሽነታችንንም አድማስ ማጉላት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም በቤተ መጽሃፍቱ የአካባቢው ማህበረሰብና መረጃ የሚፈልግ ማንኛውም ግልሰብ ተጠቃሚ ከማድረግ አኳያ ሰፊ ስራ ተሰርቷል፡፡ በዚህ መሰረት ከማህበረሰብ ተገልጋይ ብቻ ወንድ = 953 ሴት= 1332 ጠቅላላ ድምር= 2,385 ግለሰቦች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
የአያት ጨፌ ቅርንጫፋችን የቤተ-መጽሐፍት አገልግሎት ሰዓታት
ከሰኞ እስከ አርብ
ጠዋት ከ2፡30-7:00
ከሰዓት ከ7፡30-2፡00
እሁድ እና ቅዳሜ
ጠዋት ከ2፡30-7:00
ከሰዓት ከ7፡30-2፡00